በታዳጊ ፋጡማ ኡጋስ የተፈጸመውን በቡድን አስገድዶ መድፈር እና ግድያ በጥብቅ የመቃወም አቤቱታ

በታዳጊ ፋጡማ ኡጋስ የተፈጸመውን በቡድን አስገድዶ መድፈር እና ግድያ በጥብቅ የመቃወም አቤቱታ

Started
September 22, 2023
Signatures: 5,714Next Goal: 7,500
Support now

Why this petition matters

Started by Addis Powerhouse

በታዳጊ ፋጡማ ኡጋስ ላይ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ወረዳ 13 አካባቢ የተፈፀመው በቡድን መደፈር እና በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ በሴቶች መብቶች ላይ የምንሰራ መንግስታዊ ያልሆንን ድርጅቶች፣ ማህበሮች እና ህብረቶች እንዲሁም ጥቃትን የምናውግዝ ዜጎች እጅግ አሳዝኖናል፡፡ 

አስገድዶ መድፈር፣ የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች፣ የግዳጅ ጋብቻ እና ያለእድሜ ጋብቻ የመሳሰሉት ጥቃቶች አሁንም  በቤት ውስጥ፣ በስራ ቦታ፣ በመንገድ ላይ፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሆስፒታሎች እና በሌሎች በርካታ ቦታዎች በሚያስደነግጥ ሁኔታና ፍጥነት መፈጸሙ እጅግ  ያሳስበናል። 

በሴቶች፣ ታዳጊዎች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ  እየጨመሩ  ሴቶች ፣ ታዳጊዎች እና ህጻናትን የአስገድዶ መድፈር  እና የወሲባዊ ትንኮሳ ኢላማዎች እየሆኑ  በጥቃቱም ሞት ፣ የአካል እና የአእምሮ ጉዳት  እያስከተሉ ይገኛሉ፡፡ 

በኢትዮጵያ ሴቶችና ልጃገረዶች በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት እና  በሌሎች ቦታዎች በነፃነት የመኖር መብታቸውን ለማረጋገጥ፣  ለመጠበቅ እና ጥቃት ፈጻሚዎችን ለህግ ለማቅረብ  መንግስት የሴቶችን ሰብአዊ መብቶች በተመለከተ   በተደረጉ አህጉራዊ እና አለምአቀፍ ስምምነቶች፣ በተለይም በሴቶች ላይ የሚደረጉ ሁሉንም አይነት መድልዎ ለማስወገድ የወጣውን ስምምነት (CEDAW) (1979) የገባላቸውን ቃል ኪዳኖች ሙሉ በሙሉ የፈረመ። የሲቪልና የሰብአዊ መብቶች መግለጫ (1993); የቤጂንግ መግለጫ እና የድርጊት ምርሀግብር(1995)፣ የሚሊኒየም መግለጫ (2000); እና በአፍሪካ የፆታ እኩልነት መግለጫ (2004)  እንዲሁም  የሀገር ውስጥ ሕጎች እንደ ሕገ መንግሥት፣ የወንጀል ሕግ፣ የፍትሐ ብሔር ሕግ እና ሌሎች በፌደራልና በክልል ደረጃ ያሉ ሕጎች መሰረት በማድረግ ተግባራዊ የማድረግ  ሀላፊነት አለበት፡፡

በኢትዮጵያ የሴቶች መብት ተሟጋቾች እንዲሁም ሌሎች በሴቶች፣ በታዳጊ ሴቶችና ህፃናት መብቶች ላይ የምንስራ መንግስታዊ ያልሆንን ድርጅቶች ከመንግስት ጋር በመተባበር ይህንን በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት እና ወንጀል  ለመከላከል  የተለያዩ ተግባራት እና ጥረቶች ቢደረጉም ወንጀለኞች  በቅጣት ሳይቀጡ ወይም ተመጣጣኝ ቅጣት ባለማግኘታቸው  እያሳዘነን ነው።  የድርጊቱ ፈጻሚዎችም  ከድርጊታቸው እንዳይታቀቡ አድርጎአቸዋል ብለንም እናምናለን፡፡ 

በታዳጊ ፋጡማ ኡጋስ የተፈጸመውን በቡድን አስገድዶ መድፈር እና ግድያ  በጥብቅ በመቃወም የሚከተሉትን እንጠይቃለን፦

  1. መንግስት ወንጀለኞችን በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ፤
  2. በህብረተሰባችን ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስወገድ መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሰራ፤
  3. የፍትህ አካላት፣ አቃብያነ ህጎች እና ህግ አስከባሪዎች በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የስርዓተ-ፆታ ስሜትን እና ግንዛቤን በመያዝ እንዲሰሩ፤
  4. የመገናኛ ብዙሃን በሴቶች እና ህጻናት ላይ  የሚደርሱን ጥቃቶች እና ወንጀሎች ለመከላከል ህብረተሰቡን የማስገንዘብ ስራ በተከታታይ እንዲሰሩ

በሴቶች፣ ታዳጊዎች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ!


Organizations forwarding this call include: Ethiopian Women Rights Advocates ( EWRA);  Center For Advancement of Rights and Democracy (CARD); Setaweet Movement; Association Human Rights in Ethiopia; Network of Ethiopian Women Association (NEWA); Addis Powerhouse; ያንቺ Hub Consultancy Services; Sara Justice From All women Association; Ellilta Women at Risk (EWAR); Nikat Charitable Association; Finote Rehabilitation for Women with Disabilities Association; Support street children and Mother (SSCM); Women for Change; Siiqqee Women's Development Association; Engender Health; Qumen; Kal NGO Organisation; Ethiopian Women Lawyers Association (EWLA) 


         

Support now
Signatures: 5,714Next Goal: 7,500
Support now
Share this petition in person or use the QR code for your own material.Download QR Code